በካሊፎርኒያ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተሠሩ ቤቶች ትኩረትን ስበዋል
Your browser doesn’t support HTML5
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቅን ተከትሎ፣ እ.አ.አ ከ1945 እስከ 1969 ባሉት ዓመታት፣ በአሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ውስጥ በምትገኘው በፓልም ስፕሪንግስ ከተማ፣ የሥነ ሕንጻ ሥር ነቀል ለውጥ ተካሒዷል።
በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ፣ ዐዲስ ዘዴን የተከተሉ ሕንጻዎች፣ “ዘመናዊ የክፍለ ዘመኑ አጋማሽ ሕንጻዎች” ይሏቸዋል፡፡ ከሲሚንቶ፣ ብረት፣ መስተዋት እና የዕንጨት ቁሶች ፈጠራ በተቀላቀለበት ንድፍ በብዛት ተሠርተዋል።