አል ቡርሃን ጦርነቱን በአስቸኳይ ማቆም እንደሚሹ በግብጽ ጉብኝታቸው ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

የሱዳን ጦር ሠራዊት አዛዥ እና አገሪቱን በኦፊሴል የሚያስተዳድረው ጊዜያዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ጀነራል አብደል ፋታሕ አል-ቡርሃን፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ፣ በግብጽ የባሕር ዳርቻ በምትገኘው የኤል አላሚን ከተማ፣ ከአገሪቱ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታሕ አል-ሲሲ ጋራ ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

የአል-ቡርሃን የግብጽ ጉብኝት፣ ጦርነቱ በሱዳን ከተጀመረበት ካለፈው ሚያዝያ ወር ወዲህ፣ የመጀመሪያው የውጪ ሀገር ጉብኝት ነው፤ ተብሏል። ጀነራሉ፣ በግብጹ አል-ሲሲ፣ ለአንድ ሀገር መሪ የሚደረግ የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ ሠራዊታቸው፣ ለብቻው ሥልጣንን የመቆጣጣር ፍላጎት እንደሌለው የገለጹት አል ቡርሃን ተናግረዋል። ዋናው ግባቸውም፣ ለአራት ወራት የቆየውን ጦርነት በአስቸኳይ ማቆም እንደኾነ አክለዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ)