የማላዊ መንግሥት የስደተኞችን የ”ኮንቴይነር” መደብሮች ወረሰ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

የማላዊ መንግሥት፣ በሀገሩ፣ ከመጠለያ ውጪ የሚኖሩ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ “ኮንቴይነር” በሚባሉት በመርከብ ዕቃ መጫኛዎች የሚሠሩባቸውን 125 መደብሮች ወይም መጋዘኖች ወርሷል፡፡ “ከዛሬ ሰኞ ጀምረን፣ ከፍተን መፈተሽ እንጀምራለን፤” ሲል አስታውቋል። የማላዊ ፖሊስ፣ ኮንቴይነሮቹ የተወረሱት፥ “የጦር መሣሪያዎች እና ሕገ ወጥ ገንዘብ ማተሚያ የመሳሰሉ ቁሳቁሶች፣ በድብቅ ተከማችተውባቸዋል፤ የሚል ጥርጣሬ ስላለን ነው፤” ብሏል።