የፌዴራል ዳኛው የትረምፕ ክሥ የሚታየበትን ቀነ ቀጠሮ ቆረጡ
Your browser doesn’t support HTML5
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ እ.አ.አ በ2020 የተደረገውን ምርጫ ውጤት ለመቀልበስ ሞክረዋል፤ በሚል የቀረበባቸው ክሥ፣ በፍርድ ቤት የሚታይበት ቀጠሮ፣ በመጪው የፈረንጆቹ መጋቢት 4 ቀን 2024 እንዲኾን አንድ የፌዴራል ዳኛ ቀን ቆርጠዋል።
ይህም፣ ታሪካዊውን የፍርድ ሒደት፣ በፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ዘመቻው መሀከል እንዲኾን ያደርገዋል።