የአሸንዳ በዓል አክባሪ የትግራይ ልጃገረዶች “እንደ ሰላም ምንም የለም” ይላሉ

Your browser doesn’t support HTML5

የትግራይን ክልል ባንዴራ የያዙ ልጃገረዶች እና ሴቶች፣ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ዐዲስ አበባ፣ ባህላዊውን የአሸንዳ ጫወታ ሲጨፍሩ ይታያሉ። ትዕይንቱ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የማይታሰብ እንደነበር፣ የፈረንሳዩ ዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ አውስቷል፡፡

የፌዴራል መንግሥቱ፣ በህወሓት ላይ ጦር እንዲመዝ ባደረገው የሁለት ዓመቱ ግጭት ወቅት፣ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙም፣ ዘገባው ያትታል።

የኤ-ኤፍ-ፒ ዘገባ አያይዞም፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት(ፍልሰታ ለማርያም) መታሰቢያ የኾነውንና የሁለት ሳምንት ጾም ፍጻሜን መነሻ ያደረገውን የአሸንዳ በዓል፣ ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው ባህላዊ አከባበሩ እየጎላ እንደመጣ ይተርካል።

በዐዲስ አበባ ሚሌኒየም አዳራሽ በተካሔደው ሥነ በዓል ላይ ከተገኙ የአከባበሩ ተሳታፊዎች የተወሰኑት፣ የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።