በስልጤ ዞን የኩተሬ ወረዳ እንዲዋቀር “የተገባልን ቃል አልተከበረም” ያሉ ነዋሪዎች ሰልፍ ወጡ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ “የወረዳ መዋቅር ጥያቄያችን እንደሚመለስ የተገባልን ቃል አልተከበረም” ሲሉ ፣ በስልጤ ዞን አልቾ ወረዳ በኩተሬ ከተማ እና በዙሪያው የሚገኙ ነዋሪዎች፣ ቅሬታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ።

ኩተሬ ከተማ በወረዳ ደረጃ እንዲቋቋም የጠየቁት ሰልፈኞቹ፣ ሕገ መንግሥታዊ መብታችን እንዳልተከበረ ገልፀው ዐዲሱ ክልል በኢ-ፍትሐዊነት ኮንነዋል።

የቀደመው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በመፍረሱ እና ዐዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስትዳደሩ ገና ባለመዋቀሩ ጉዳዩ የሚመለከተውን የአካብባኢው ባለሥልጣን አግኝተን በሰልፈኞቹ ቅሬታ ላይ ያላቸውን ምላሽ ማካተት አልቻልንም።

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር አቶ ማሩፍ አልቶ፣ የነዋሪዎቹ ጥያቄ ባልተወሳሰበ ፖለቲካዊ ውሳኔ ካልተፈታ፣ በሕዝብ እና በመንግሥት መካከል፣ አለመተማመንን በማባባስ ተቃውሞ እንዳያስከትል አሳስበዋል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።