የጎሮ ዶላ ወረዳ በምሥራቅ ቦረና ዞን ሥር መደራጀቷን በሰልፍ በተቃወሙ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል፣ ዐዲስ በተዋቀረው ምሥራቅ ቦረና ዞን ሥር ያለአግባብ ተካላለች በተባለችው የጎሮ ዶላ ወረዳ፣ ከመንፈቅ ዓመት በፊት የተነሣው ተቃውሞ ተባብሶ፣ ሰልፍ ከወጡ ነዋሪዎች መካከል፣ ስድስት ሰዎች እንደተጎዱ፣ የጤና ተቋም ምንጮች እና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ለተቃውሞ ከወጡት ሰልፈኞች መካከል፣ ከ200 በላይ የሚደርሱ ሰዎች እንደታሰሩ ፣ ዛሬም በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ላይ እንደኾኑ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የወረዳዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የጎሮ ዶላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌቱ ጩሉቄ ደግሞ፣ ትላንት የተሞከረ የተቃውሞ ሰልፍ እንደነበረ አረጋግጠው፣ በጸጥታ ኀይሉ ርምጃ እንደበተነ ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከምሥራቅ ቦረና እና ከኦሮሚያ ክልል ኮምዩኒኬሽንስ ቢሮ መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።