በትግራይ ክልል በሀገራዊ ምክክር ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲጀመር ኮሚሽኑ ጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል በሀገራዊ ምክክር ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲጀመር ኮሚሽኑ ጠየቀ

በትግራይ ክልል፣ በሀገራዊ ምክክር ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲጀመር፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በደብዳቤ እንደጠየቀው አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ፣ በትላንትናው ዕለት፣ በዐዲስ አበባ ከተማ፣ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች ልየታ መጀመሩንና የልምድ ልውውጥ መድረክ ማዘጋጀቱን፣ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ይኸው፣ የምክክር ጉባኤው አስተባባሪዎች እና ተሳታፊዎች ልየታ ሒደት፣ በተቀሩትም ክልሎች እንደሚቀጥል ያመለከቱት ዶ/ር ዮናስ፣ በዐማራ ክልል የተስፋፋው ግጭት ግን፣ በሥራችን ላይ ተጽእኖ አሳድሯል፤ ብለዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።