ኢትዮጵያ ብሪክስን በአባልነት ልትቀላቀል ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ብሪክስን በአባልነት ልትቀላቀል ነው

በምኅጻረ ቃሉ ብሪክስ በመባል የሚታወቀው የአምስት ፈጣን አዳጊዎች ሀገራት ቡድን፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገራትን በአባልነት ለመቀበል ወስኗል፡፡

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ውሳኔውን፥ “ለአገራችን ታሪካዊ ኹነት ነው፤” ብለዋል።

ብሪክስን ኢትዮጵያን በአባልነት የተቀበለበት መስፈርት ምን ሊኾን እንደሚችልና በአባልነት ፋይዳው ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ፣ የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎቹ አቶ ክቡር ገና እና ፕር. ዓለማየሁ ገዳ፣ የተለያዩ ሐሳቦችን አንጸባርቀዋል፡፡

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ፣ ኢትዮጵያ በአባልነቷ፥ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ልታገኝ እንደምትችል ሲያመላክቱ፤ አቶ ክቡር በበኩላቸው፣ ብሪክስ ለኢትዮጵያ፣ በአጭር ጊዜ ሊያስገኝ የሚችለው ብዙም ጠቀሜታ እንደሌለ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።