በኢትዮጵያ የሸማቾች ጥበቃ ሕጎች ባለመተግበራቸው ማኅበረሰቡ ለከፍተኛ እንግልት እንደተዳረገ ተሟጋች ድርጅቱ ገለጸ
Your browser doesn’t support HTML5
የሸቀጦች እና የአገልግሎቶች የዋጋ ንረት የመጨረሻው ጫና የሚያርፈው በሸማቹ ላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ እየተባባሰ ከመጣው የኑሮ ውድነት ጋራ፣ የሸማቹ ማኅበረሰብ መብት እንዳልተከበረና በዚኽም ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረገ እንዳለ፣ የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ዋና ዲሬክተር አቶ ቁምላቸው አበበ ይናገራሉ፡፡