"ሰማያዊ እና ግራጫ - ይህ የስደት ዘመን" አውደ ርዕይ

Your browser doesn’t support HTML5

በቅርቡ ዋሽንግተን ላይ ለእይታ የበቃ አውደ ርዕይ ነው። እውቋ ባለ ብዙ ዘርፍ የሥነ ጥበብ ባለሞያ፡ ሰዓሊ፣ ቀራጺ፣ ገጣሚ እና መምህርት ከበደች ተክለአብ ከሌላ ታዋቂ አሜሪካዊ ባለ ቅኔ ጋር በትብብር ያሳየችው ነው።

በተለይ በስደት እና ከቀያቸው ተጥለው ለፍልሰት የተዳረጉ አያሌዎች ከመንገዳቸው የሚገጥማቸውን መከራ እና እንግልት፤ ከሚኖሩበት መንደር በአካል ባይርቁም ባሉበት የተዘነጉትን እጣና የሕይወት ምስቅልቅል ጭምር የሚቃኙ ጥበባዊ ሥራዎች ናቸው።

በዋሽንግተኑ የአሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መዘክር እንደ አውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ከሰኔ 17/2023 እስከ ነሃሴ 13/2023 ሁለት ወራት ለተቃረበ ጊዜ በታየው አውደ ርዕይ ለእይታ የቀረቡ ሥራዎችን እና የዝግጅቱን መነሻዎች ጨምሮ የሚያስቃኘውን ሰዓሊ ከበደች ተክለአብ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ከተያያዘው የድምጽ ማጫወቻ ይከታተሉ።