በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ተከሳሾች የረሃብ አድማ ማድረጋቸው ተገለጠ

Your browser doesn’t support HTML5

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ተከሳሾች ለሦስት ቀናት የሚቆይ የረሃብ አድማ ማድረጋቸውን የቤተሰብ አባላት ገለጹ።

የረሀብ አድማውን የሚያደርጉት “በአማራ ክልል በንፁኃን ላይ እየደረሰ ነው ያሉትን ግድያና ሌሎች ጥቃቶች፤ እንዲሁም “በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ነው ያሉትን እስር” በመቃወም መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙት የፌደራል እና የክልል ምክር ቤት አባላት እንደዚሁም ሌሎች ግለሰቦች "ከነበሩበት ስፍራ ወደ ማይታወቅ ቦታ ተወስደዋል" ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል ፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ከታሳሪ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሰለሞን ገዛኸኝም አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ከመንግሥት አካላት ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ግን አልተሳካም።

ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡