በዐማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ቀጥሏል

Your browser doesn’t support HTML5

አብዛኛው የዐማራ ክልል አካባቢዎች፣ ወደ ሰላማዊ ኹኔታ ተመልሰው መደበኛ እንቅስቃሴ ቢጀመርም፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የጨረቃ አካባቢ እና በምሥራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ዐማኑኤል ከተማ፣ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል፣ የተኩስ ልውውጥ እየተካሔደ እንደሚገኝ፣ ነዋሪዎች ለቪኦኤ ገለጹ።

በተኩስ ልውውጡ፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን፣ ነዋሪዎቹ አክለው ተናግረዋል። በሌላ በኩል፣ ግጭቱ፣ የሰብአዊ ርዳታንና በቅርቡ የተከሠተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እንዳስተጓጎለው፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ይከታተሉ።