የሶማሊያ የጠረፍ ከተሞች በአሸዋ ማዕበል እየተዋጡ ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

ሆቢዮ የምትባለው፣ የሶማሊያ ከተማ ነዋሪዎች፥ መኖሪያ ቤቶቻችን፣ ትምህርት ቤቶቻችንና መደብሮቻችን፣ በአሸዋ ማዕበል እየተዋጡ ነው፤ ሲሉ አሳሰቡ፡፡ “የጠረፍ ከተሞች ህልውናም አደጋ ላይ እየወደቀ ነው” ሲሉም ስጋታቸውን ገለጹ፡፡

11ሺሕ ሕዝብ ያላት የሆቢዮ ከተማ ከንቲባ ኦስማን አሕመድ አብዱሌ፣ የአሸዋውን ማዕበል የቀሰቀሰው የአየር ንብረት ለውጡ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው የሚፈጸመው የደን ጭፍጨፋ እና ድርቁም፣ አስተዋፅኦ እያደረጉ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

የሆቢዮ ከተማ ነዋሪዎች፣ “ከተማችንን በኀይለኛ ነፋስ ታዝሎ የሚመጣው አሸዋ እየዋጣት፣ ዐይናችን እያየ ከተማችን እየጠፋች ነው፤” ሲሉ አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ይከታተሉ።