በኦሮሚያ ክልል “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ለማሠሥ” በሚል ይፈጸማል ያሉት ግድያ እንዲቆም ኦነግ እና ኦፌኮ ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች፣ “የኦሮሞ ነፃነት ታጣቂዎችን ለማሠሥ” በሚል የሚንቀሳቀሱ የጸጥታ ኀይሎች፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያደርሳሉ ያሉትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዲያቆሙ ጥሪ አቀረቡ።

በሌላ በኩል፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጮቢ ወረዳ፣ ባለፈው ሳምንት፣ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች በመንግሥት ኀይሎች እንደተገደሉ፣ አንዳንድ የዐይን እማኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

በጉዳዩ ላይ፥ ከዞን፣ ከኦሮሚያ ክልል እና ከፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለአሁኑ አልተሳካም።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን ጮቢ ወረዳ፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ እንደተፈጸመ ስለተገለጸው ግድያ፣ መረጃ እያሰባሰበ እንደኾነ ጠቅሶ፣ ምርመራ ለማከናወን፣ የአካባቢው የጸጥታ ኹኔታ እንደሚያዳግት አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።