ኤኮዋስ በኒዤር ወታደራዊ ጣልቃ ገብ ርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በኒዤር፣ በስዒረ መንግሥት ሥልጣን በያዘው ሁንታ ጉዳይ፣ በናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃ ላይ የተነጋገሩት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ(ኤኮዋስ) የመከላከያ ሚኒስትሮች፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን ለመመለስ፣ ሊወሰድ የሚችል ወታደራዊ ጣልቃ ገብ ርምጃ በማቀድ ላይ እንደኾኑ አረጋግጠዋል፡፡

የኒዤር ፕሬዚዳንታዊ ዘብ ወታደሮች፣ ፕሬዚዳንት መሐመድ ባዙምን፣ ባለፈው ሐምሌ 26(እአአ) ከሥልጣናቸው አስወግደው አስተዳደሩን ተቆጣጥረዋል፡፡

ቲመቲኦቢየዙ ከአቡጃ ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ታቀርበዋለች፡፡