ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻ፣ የጎሮዶላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ 14 አመራሮች፣ የምሥራቅ ቦረና ዞን መዋቀሩን ተከትሎ፣ ሕዝብን ለተቃውሞ አነሣስታችኋል፤ ተብለው በእስር ላይ እንደሚገኙ፣ ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ስለምን ተፈጻሚ እንዳላደረገ፣ ከጎሮዶላ ወረዳ፣ ከምሥራቅ ቦረና ዞንና ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምላሽ እና አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት፣ ለጊዜው አልተሳካም።
ባለፈው የካቲት ወር፣ በክልሉ ምክር ቤት ውሳኔ፣ ዐዲስ በተዋቀረው የምሥራቅ ቦረና ዞን፣ ወረዳዋ አለመካተቷ፣ ለተቀሰቀሰው ተቃውሞ ዋና መንሥኤ እንደኾነ የሚናገሩ ነዋሪዎች፣ ችግሩ እስከ አሁን አለመቀረፉን አመልክተዋል፡፡