ጦርነት ያባባሳቸውን አጉል ልማዶች የምታጠና ወጣት የሕግ ባለሞያ

Your browser doesn’t support HTML5

ኩልሱም ኑር፥ በኢትዮጵያ፣ የሕፃናት እና ሴቶች መብትን የሚመለከቱ ሕግ ነክ ምርምሮችን ያደረገች ባለሞያ ናት። ከሕግ ባለሞያነቷ ጎን ለጎን፣ በልዩ ልዩ ብዙኀን መገናኛዎች አበርክቶዋ፣ ማኅበረሰባዊ ንቃትንና ግንዛቤን ለማዳረስ ትጥራለች። ከዘንድሮዎቹ፣ የማንዴላ ዋሺንግተን "ያሊ 2023" የወጣት መሪዎች ትስስር መርሐ ግብር ተሳታፊዎች መካከል አንዷ የነበረችው ወጣት፣ በሚቺጋን ስቴትስ ዩኒቨርስቲ፣ የቀለም ትምህርት እና አመራር ሥልጠናዎችን ለሳምንታት ወስዳለች።