ወደ አደባባይ ወጣ ብላ ድንገት ከመንገድ የምትተዋወቃቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ሕይወት በቅርበት ለመጋራት ጥረት የምታደርግበትን ልዩ የቴሌቭዥን ፕሮግራም በቅርቡ አስተዋውቃለች።
የሌሎችን ፈተና የበዛው ህይወት እንደ ሰው ቀርቦ እና ጊዜ ወስዶ ለመረዳት የፈቀደ ነጻ መንፈስ የሚንጸባረቅበትን ይህን ዝግጅቷን “ኢትዮጵያዬ” የሚል መጠሪያ ሰጥታዋለች።
ከራዲዮ መጽሄቶቹ ቆንጅት ታዬ እና አሉላ ከበደ ጋር በነበራት ቆይታ ስለ ሞያ ህይወት ጉዞዋ እና በአዲሱ የቴሌቭዥን ቅንብርዋ ማሳካት ስላለመችው ቁም ነገር ታጋራለች።