ለሥነ ጽሁፍ እና ሳይንስ ያደረ ልብ። የአራት የዓለም ገናና የፍልስፍና፣ የስነ ልቦና እና የሥነ ጽሁፍ አዋቂዎችን እምነት እና አስተሳሰብ የሚመረምረውን አብይ ሥራውን ጨምሮ የበርካታ ልቦለድ እና ሞያ ነክ መጻሕፍት ደራሲ ነው።
በመደበኛ ሞያው ደግሞ በጀርመኗ ድሬስደን ዩኒቨርሲቲ የኮምውተር ኔት ወርክ መምሕር እና ተመራማሪ ነው። ፕሮፌሰር ዋልተንጉስ ዳርጌ። ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረገው ቆይታ ስለ ሕይወት እና ሥራው ያወጋናል።
ሙሉውን ምልልሳችንን ከተያያዘው የድምጽ ማጫወቻ ይከታተሉ።