የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል

Your browser doesn’t support HTML5

ዛሬ አመሻሽ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የተወያዩት የዓለም ባንክ ፕሬዝደንት፣ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ ለወጣቶችና ለሴቶች የስራ እድል የሚፈጥሩ ዘርፎችን ይጎበኛሉ፡፡

ባንጋ ጉብኝታቸውን የጀመሩት የዓለም ባንክ እና ኢትዮጵያ የ400 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ከተፈራረሙ ከቀናት በኋላ መሆኑ ነው ፡፡

በዓለም ባንክ ድጋፍ የተገነባውን ቦሌ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክ በነገው እለት እንደሚጎበኙም ታውቋል፡፡