ኅብረተሰቡን በተገቢው ባለማገልገላችን በድለናል ያሉ የሲዳማ ክልል ሠራተኞች በሰልፍ ይቅርታ ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

- “በሰልፍ ሳይኾን ሕግንና መመሪያን በአገባቡ በማስፈጸም ነው”-ምሁራንና ነዋሪዎች

የሲዳማ ክልል እና የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች፣ ዛሬ፣ በሐዋሳ ከተማ ባካሔዱት ሰልፍ፣ ለኅብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት አልሰጠንም፤ ሲሉ ይቅርታ ጠየቁ።

ሠራተኞቹ በዛሬው የይቅርታ ሰልፋቸው፣ በኅብረተሰቡ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይዘወተራሉ ያሏቸውን በደሎች በዝርዝር ተናግረዋል፡፡ ብልሹ አሠራር፥ ጉቦ መቀበል፥ ባለጉዳይን ማጉላላት እና የመንግሥትን የሥራ ሰዓት መስረቅ፣ በሠራተኞች የሚዘወተር ወንጀል ነው፤ ብለዋል ሰልፈኞቹ፡፡

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት፣ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል መምህር እና የውጭ ግንኙነት ዲሬክቴር ረዳት ፕሮፌሰር ዮሐናን ዮካሞ በበኩላቸው፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ በሠራተኛ እና አሠሪ ሕግ እና መመሪያ የሚፈታ እንጂ፣ በሰልፍ የሚመለስ እንዳልኾነ ተናግረዋል።

ዝርዝርን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።