በጋሞ “ዱቡሻ” ባህላዊ የአደባባይ እርቅ ከሁለት ሺሕ በላይ ክሦች እልባት እንዳገኙ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን፣ ወደ ፍርድ ቤት ከቀረቡ በርካታ የወንጀል እና የፍትሐ ብሔር የክሥ መዝገቦች ውስጥ፣ ከሁለት ሺሕ በላይ የሚኾኑቱ፥ “ዱቡሻ” በተሰኘው የጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ የአደባባይ ዳኝነት እና እርቅ ሥርዐት እንደተፈቱ፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

በጋሞ ባህላዊ የግጭት አፈታት ላይ፣ ምርምር ማድረጋቸውንና በባህላዊ የግጭት አፈታት እና የሰላም ግንባታ ላይ መጽሐፍ ማሳተማቸውን የተናገሩት፣ የአስተዳደር እና የልማት ጥናት ምሁር አቶ ዘነበ በየነ፣ “ዱቡሻ”፥ የባህላዊ አስተዳደር ሕግ የሚወጣበት፣ የሚሻሻልበት፣ በዳዮች እና ተበዳዮች የሚዳኙበት የፍትሕ አደባባይ ወይም ሸንጎ እንደኾነ አስረድተዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።