ዘለንስኪ የክራይሚያ ድልድይ ጥቃት ተቀባይነት ያለው እንደነበረ ተናገሩ

ዘለንስኪ የክራይሚያ ድልድይ ትክክለኛ የጥቃት ዒላማ እንደነበረ ተናገሩ

ዘለንስኪ የክራይሚያ ድልድይ ትክክለኛ የጥቃት ዒላማ እንደነበረ ተናገሩ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የክራይሚያ ድልድይ የጥቃት ዒላማ መሆኑ ትክክለኛ(ተቀባይነት ያለው) እንደነበር ተናገሩ ።

ክራይሚያን ከሩሲያ ጋር የሚያገናኘው ድልድይ ሰኞ ዕለት የፈንጂ ጥቃት ከደረሰበት በኃላ የተወሰነ ክፍሉ ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል ።በፍንዳታው ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ውስጥ እየተካሄደ በሚገኘው የየአስፐን የፀጥታ ጉባኤ ላይ በቪዲዮ መገናኛ ንግግር ያደረጉት ዘለንስኪ ፣“ይህ በየለቱ ለጦርነቱ የሚሆን መሳሪያ የሚቀርበበት መስመር ነው። የክራይሚያን የባህር ገብ መሬትም የጦር ቀጠና አድርጎታል ” ብለዋል ።

ዩክሬን ለድልድዩ ጥቃት ኃላፊነቱን አልወሰደችም። ሞስኮ ግን ድልድዩ ላይ ለተከፈው ጥቃት ዩክሬንን ከሳለች ።ዘለንስኪ በትናንቱ ንግግራቸው ፣ “ሩሲያ ዛሬ ሁለት ተጨማሪ ልጆችን ገድላለች። በ 2007 የተወለደች ሴት እና በ 2013 የተወለደ ወንድ ልጅ ” ሲሉም አክለዋል ።

ዘሌንስኪ ልጆቹ የተገደሉት በዶኔትስክ ክልል ድሩዝባ መንደር ላይ በተፈጸመ ጥቃት መሆኑን ገልጸዋል። በጥቃቱ ሁለት ሴቶች ሲሞቱ የባህል ማዕከል፣ ትምህርት ቤት እና የመኖሪያ ሕንፃዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።