ድርቅ በተጎዱ የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት ጠቃሚ አማራጭ እንደኾነላቸው አምራቾች ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

ዝናም አጠር በኾኑና ድርቅ ከብቶቻቸውን በአሳጣቸው የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች፣ ከአንድ ዓመት በፊት የተጀመረው፣ የ30-40-30 የፍራፍሬ ፕሮጀክት፣ ጥቅም እያስገኘላቸው እንደኾነ፣ ፕሮጀክቱ አስቀድሞ የተጀረበት የደቡብ ኦሞ ዞን አርሶ እና አርብቶ አደሮች ተናገሩ።

የ30-40-30 የፍራፍሬ ፕሮጀክት፣ በክልሉ የሚገኙ አርሶ እና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሲባል፣ ከአንድ ዓመት በፊት የተጀመረ ነው፡፡ በፕሮጀክቱ መሠረት፣ አንድ አርሶ ወይም አርብቶ አደር በማሳው ላይ፣ አንድ መቶ የፍራፍሬ ችግኞች ይኖሩታል፡፡

ትምህርት ቤቶች እና ሃይማኖታዊ ተቋማት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎችም፣ እስከ 10ሺሕ የፍራፍሬ ዛፎች እንዲኖራቸው የሚያስችል ፕሮጀክት እንደኾነ፣ የሐሳቡ አመንጪ እና የክልሉ የግብርና ቢሮ ሓላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።