ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ቀሪ ያደረገው አከራካሪው የኅዳጣን ማኅበረሰቦች አዎንታዊ ድጋፍ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፥ ጥቁሮችን፣ ሴቶችንና ሌሎች ኅዳጣን የማኅበረሰብ ክፍሎችን ጨምሮ፣ በአሜሪካ የሀብት ድልድል ተካፋይ ያልኾኑ ወይም በማንነታቸው አድልዎ ተፈጽሞባቸዋል ተብለው የሚታሰቡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ፣ ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን፣ የዘር ልዩነትን ያገናዘበ የአዎንታዊ ድጋፍ የመመልመያ ፖሊሲ(Affirmative Action)፣ ከዚኽ በኋላ ቀሪ የሚኾንበትን ውሳኔ አሳልፏል።
በርዕዮተ ዓለም መስመር የተከፋፈሉት የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ ስድስት ለሦስት በኾነ ድምፅ፣ ላለፉት 45 ዓመታት በሥራ ላይ የኖረውን ፖሊሲ መቀየራቸው፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚኖረው የትምህርት ዕድል እና የዘር ስብጥር ላይ፣ ምን ዐይነት ተጽእኖ ይኖረዋል? በሚል መጠየቅ ባለሞያን አነጋግረናል፡፡

እንግዳችን አቶ ዘካርያስ ኀይሉ፣ በሚኖሶታ የከተማ ምክር ቤት፣ የፍትሐዊነት እና የእኩል ዕድል ቢሮ ረዳት ዲሬክተር እና የሕግ ባለሞያ ናቸው፡፡

አስተያየታቸውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።