ሩሲያ ለማሊ ድጋፍ እንደምትሰጥ አስታወቀች

በማሊ የተመድ የሠላም አስከባሪ ኃይል አባል (ፎቶ ፋይል / ኤኤፍፒ)

የተመድ የሰላም ልዑክ በማሊ ያለው ተሳትፎ መጠናቅቁን ተከትሎ፣ ሩሲያ ለአገሪቱ “የማያቋርጥ ድጋፍ” እንደምጸጥ መግለጿን የማሊ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት አስታውቋል።

የጸጥታው ም/ቤት በማሊ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ መወሰኑን ተከትሎ፣ የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አገራቸው “በወታደራዊ፣ ሰብዓዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ መስክ ለማሊ የምታደርገውን የማያቋርጥ ድጋፍ ታድሳለች” ሲሉ ቃል መግባታቸውን የማሊው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በማሕበራዊ ሚዲያ በለቀቀው መልዕክት አስታውቃል።

በማሊ የሚገኘው ወታደራዊ ሁንታ ከሩሲያ ጋር ካበረ በኋላ በአገሪቱ የሚገኘው የተመድ ሠላም አስከባሪ ኃይል እንዲወጣ ጠይቋል።

የማሊው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አብድላዬ ዲዮፕ ከሁለት ሣምንት በፊት የተመድ ልዑክ ሥራው በመክሸፉ አገራቸውን ጥሎ እንዲወጣ የጸጥታውን ም/ቤት ጠይቀዋል። ም/ቤቱ በትናንት ዓርብ ውሎው በማሊ የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲወጣ በአንድ ድምጽ ወስኗል።

በማሊ የሚገኘው ሁንታ ከሞስኮ ጋር በመወገን የሩሲያን ቅጥር ወታደራዊ ቡድን ቫግነር ወደ አገሪቱ አስገብቶ የነበረ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት የቫግነሩ ቡድን በሩሲያ መከላከያ ላይ ማመጹን ተከትሎ ግን ማሊ ለሞስኮ ያላትን አጋርነት አስታውቃለች፡፡