የተመድ ዋና ጸሃፊ ሄይቲን ጎበኙ

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ (ፎቶ ፋይል / ኤፒ)

የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሪዝ ዛሬ ሄይቲን ጎብኝተዋል። ወሮ በሎች ዋና ከተማዋን ፖርት ኦ ፕሪንስ ጨምሮ ተቆጣጥረው በፈጠሩት ሁከት እና ዝርፊያ ችግር ላይ የወደቀችው አገር ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝ ነው ተብሏል።

የሄይቲ መንግስት ከዘጠኝ ወር በፊት ሰላም አስከባሪዎች ከሌሎች አገሮች ተልከው አገሪቱን እንዲያረጋጉ ያቀረበውን ጥሪ ጉቴሬዝ ደግፈው ነበር። ነገር ግን አንድም አገር እስከአሁን በፈቃድ ኃይሉን የላከ እንደሌለ ታውቋል።

“አጋርነቴን ለማሳየት በሄይቲ እገኛለሁ፣ ዓለምም አጋርነቱን እንዲያሳይና ዓለም አቀፍ ሃይል በመላክ የአገሪቱን ፖሊስ እንዲያግዝ ጥሪ አቀርባለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል የተመዱ ዋና ጸሃፊ።