በጎ አድራጊዎችን ያከበረ የሽልማት ሥነ ሥርዐት ተከናወነ

Your browser doesn’t support HTML5

በበጎ ምግባራቸው፣ በበርካቶች ሕይወት ላይ ደግ አሻራ የተዉ ኢትዮጵያውያንን ለማበረታት ያለመ የሽልማት ሥነ ሥርዐት ከሰሞኑ ተከናውኗል፡፡ “ጣፋጭ ሕይወት” የተሰኘው ሽልማት፣ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ለመልካም ተግባራት ያዋሉ ወጣቶችን ጨምሮ በስድስት ዘርፎች ግለሰቦችን ሸልሟል፡፡ ስለ ሽልማቱ ዓላማ እና ፋይዳ ለማወቅ፣ ሀብታሙ ሥዩም፥ የሥነ ሥርዐቱ ዋና አዘጋጅ አንተነህ ተስፋዬን አነጋግሯል፡፡