ተፈጥሮንና ፋሽንን ያሰናኘችው የልብስ ንድፍ ባለሞያ
Your browser doesn’t support HTML5
በዩናይትድ ስቴትስ፣ ሀገራዊ የእጅ ሥራ ጥበቦችን መሠረት በማድረግ፣ ልዩ ልዩ አልባሳትንና ጌጣጌጦችን ለገበያ ከሚያቀርቡ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ ተሻለች ታደሰ ኤጋ ናት። ተሻለች፣ በተለይ እንሰትንና ቃጫን ከመሰሉ ተፈጥሮአዊ ግብዓቶች በምታዘጋጃቸው ምርቶች፣ የተለያዩ ዕውቅናዎችንና ሽልማቶችን ለማግኘት በቅታለች።
ከሥራዎቿ ጋራ የተገናኙ ሐሳቦቿን ለመስማት፣ ሀብታሙ ሥዩም ከተሻለች ጋራ አጭር ቆይታ አድርጓል።