የትግራይ ተዋጊዎች 85 በመቶ ትጥቅ እንደፈቱና አደረጃጀታቸውን ማፍረሱም በኵሓ መጀመሩ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል በተደረገው የሰላም ስምምነት መሠረት፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ ተዋጊዎች፣ 85 በመቶ የጦር መሣሪያቸውን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማስረከባቸው ተገለጸ።

ዛሬ፣ በመቐለ ከተማ በተከናወነው ቀጣይ የርክክብ ሥነ ሥርዐት ላይ፣ የአፍሪካ ኅብረት ያቋቋመው፣ የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት ክትትል እና ቁጥጥር ቡድን በታዛቢነት ተገኝቷል።

በሰላም ስምምነቱ መሠረት፣ የትጥቅ ማስፈታቱን ተከትሎ የሚከናወነው፣ የተዋጊዎችን አደረጃጀት የማፍረስ ሒደት፣ በዛሬው ዕለት፣ በመቐለ ዙሪያ በምትገኘው ኵሓ መንደር፣ በታዛቢዎች ፊት በኦፊሴል መጀመሩ ተገልጿል፡፡