የዐማራን ክልልን መሪ አልባ በማድረግ ያደሩ ጥያቄዎቹን የማዳፈን አደጋ መኖሩን ርእሰ መስተዳድሩ ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የዐማራ ክልል ሕዝብ የሚያነሣቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች የሚፈቱት፣ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ነው፤ ሲሉ፣ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ይልቃል ከፋለ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ በባሕር ዳር ከተማ፣ ለክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የተዘጋጀው እና ትላንት፣ በርእሰ መስተዳድሩ ንግግር በተከፈተው መድረክ፣ ውይይት እየተካሔደ ነው።