በሱዳን የቀጠለው ውጊያ እና ወደ ቻድ የመዛመቱ ስጋት

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በሱዳን የቀጠለው ውጊያ እና ወደ ቻድ የመዛመቱ ስጋት

በሱዳን፣ ምዕራብ ዳርፉር ክፍለ ግዛት፣ እየተካሔደ ያለው ከባድ ውጊያ፣ ወደ አጎራባች ሀገራት ይዛመታል፤ የሚለው ስጋት እየጨመረ መኾኑን ተንታኞች ይናገራሉ።

ከትላንት በስተያ ረቡዕ፣ ከሱዳን ጋራ በሚያዋስነው የቻድ የድንበር አካባቢ የተገኘው የቪኦኤ ዘጋቢ፣ የተኩስ እና የፍንዳታ ድምፅ ሰምቷል፡፡ የተገደሉ ሰዎች አስከሬኖችንና ቁስለኞችንም አይቷል። የቻድ የፖሊስ አዛዥ በበኩላቸው፣ ሕዝቡ እንዲረጋጋ እያሳሰቡ መኾናቸውን፣ ለቪኦኤ ገልጸዋል። ሄንሪ ዊልክንስ ከቻድ ኩፍሩን ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

SEE ALSO: በቻድ የሱዳን ፍልሰተኞች ቁጥር በሳምንት ውስጥ በዕጥፍ ጨመረ