የኮሌራ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ተዛመተ፤ በደቡብ ክልል 18 ሰዎችን ገደለ

Your browser doesn’t support HTML5

የኮሌራ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ አራት ክልሎች መዛመቱን የጤና ሚኒስቴር ሲገልጽ፣ በደቡብ ክልል ልዩ ልዩ ዞኖች እና ወረዳዎች ደግሞ፣ 18 ሰዎችን ለኅልፈት መዳረጋቸውንና 919 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን፣ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል። ወረርሽኙ በበረታባቸው የክልሉ ዞኖች፣ ትላንት እና ዛሬ ክትባት መስጠት መጀመሩን፣ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዲሬክተር አቶ ማሙሽ ሑሴን ገልጸዋል።