የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኤክስፖርት መዳከሙ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ፣ በቅርቡ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአቀረቡት ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨትመንት ደካማ እንደኾነና አነስተኛ ውጤት ማስመዝገቡን አስታውቀዋል፡፡ የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ዶ/ር አቡሌ መሐሪ እና ዶ/ር አረጋ ሹመቴ ፣ የችግሩ መንሥኤ፥ በኮሚሽነሯ የተጠቀሱት ብቻ ሳይኾኑ፣ የአስተዳደር ብቃት ማነስ፣ አማሳኝነት እና የብቁ ሰው ኃይል እጥረት እንደኾኑ ያስረዳሉ፡፡