በኬኒያ ከሃይማኖታዊ ስብከት በተያያዘ የሞቱት ቁጥር ከ200 አለፈ
Your browser doesn’t support HTML5
በኬንያ የባሕር ዳርቻ ክፍለ ግዛት ውስጥ፣ ባለፈው ቅዳሜ፣ 22 አስከሬኖች መገኘታቸውን ተከትሎ፣ ከሃይማኖታዊ ስብከት ጋራ ተያይዞ፣ በረኀብ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 201 መድረሱ ተነገረ፡፡ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ በቁፋሮ ከተገኙት አስከሬኖች በሚበዙት ላይ፣ ለረጅም ጊዜ በረኀብ ጠኔ የመጎዳት ምልክት መታየቱን፣ የክፍለ ሀገሩ የፖሊስ ኮሚሽነር ገልጸዋል፡፡ እስከ አሁን ቤተሰቦቻቸው ያላገኟቸው፣ ከ600 የሚበልጡ ሰዎች መኖራቸውንም አመልክተዋል፡፡