በተቃውሞ የሰነበቱት የዐማራ ክልል ከተሞች ወደ አንጻራዊ መረጋጋት እየተመለሱ

Your browser doesn’t support HTML5

በተቃውሞ የሰነበቱት የዐማራ ክልል ከተሞች ወደ አንጻራዊ መረጋጋት እየተመለሱ

የሰው ሕይወት የጠፋባቸው እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ግጭቶች እና የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ሲካሔድባቸው የሰነበቱት ልዩ ልዩ የዐማራ ክልል ከተሞች፣ ወደ አንጻራዊ መረጋጋት በመመለስ ላይ እንደኾኑ፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
ዋነኛ ከሚባሉ ከተሞች በአንዳንዶቹም፣ ተዘግተው የነበሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የንግድ ድርጅቶች፣ ቀስ በቀስ ወደ ሥራ በመመለስ ላይ እንደኾኑ ነዋሪዎቹ አመልክተዋል፡፡
ለዐማራ ኮርፖሬሽንማብራሪያ የሰጡት፣ የክልሉ የብልጽግና ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ፣ መንግሥት፥ የልዩ ኃይል አባላትን “ወደ ጸጥታ ተቋማት መልሶ ለማደራጀት” ያሳለፈው ውሳኔ ተቃውሞ የገጠመው፣ “አስቀድሞ ሕዝብ እንዲወያይበት በአለመደረጉ” እንደኾነ አስረድተዋል፡፡በቀጣይ፣ ከሕዝብ ጋራ ለመወያየት ዕቅድ መያዙንም አስታውቀዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።