በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት፣ በትግራይ ክልል ውስጥ የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እና ለማደራጀት በትኩረት እንደሚሠራ፣ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶር. ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
በዛሬው ዕለት መቐለ ከተማ የገባውና በጤና ሚኒስትሯ የተመራው ልዑካን ቡድን፣ በክልሉ የሚገኙ ልዩ ልዩ የጤና ተቋማትን ጎብኝቷል፤ ከክልሉ አመራሮችም ጋራ ተወያይቷል።
ጉብኝቱን አስመልክቶ፣ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ሓላፊ ዶር. ዐማኑኤል ኃይለ፣ በጦርነቱ የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ በመገንባት እና በማደራጀት ረገድ፣ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመራሮች ጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።