የሳይንሳዊ ምርምር ጥናት ባለቤት የ15 ዓመቷ ክርስቲያን ተኮላ

Your browser doesn’t support HTML5

የሳይንሳዊ ምርምር ጥናት ባለቤት የ15 ዓመቷ ክርስቲያን ተኮላ

በዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂኒያ የምትኖረው የ10ኛ ክፍል ተማሪ እና የ15 ዓመቷ ትውልደ ኢትዮጵያ ክርስቲያን ደረጀ ተኮላ የሳይንሳዊ ግኝት ሆኖ የተመዘገበው ጥናታዊ ሥራ ባለቤት ሆናለች፡፡

ጥናታዊ ሥራው “የተለያዩ ማጽጃዎች በፍሪጅ መደርደሪያዎች ላይ ባሉ ባክቴሪያዎች እድገት የሚያሳድሩት ተጽእኖ Effects of Cleaning Agents on Bacterial Growth in Refrigerator Surfaces “በሚል ርዕስ የታተመ የምርምር ጽሁፍ ነው።

የክርስቲያን ተኮላ ስራ ለህትመት የበቃው በሃርቫርድ እና ጆን ሀፒክንስ ዩኒቨርስቲ ከሚገኙ ሁለት ተባባሪዎችዋ ጋር ነው፡፡

ጽሁፉን ያተመው ደግሞ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ባሉ ተመራቂ ተማሪዎች እና ድህረ ምረቃ (ዶክተር) ተማራማሪዎች እንዲሁም ፕሮፌሰሮች አጋዥነት የሚታተመው The Journal of Emerging Investigators (JEI) የአካዳሚ መጽሄት ነው፡፡