የኮንሶ እና የደቡብ ኦሞ ዞኖች የዘር እና የማዳበሪያ እጥረት ገጥሟቸዋል

Your browser doesn’t support HTML5

የኮንሶ እና የደቡብ ኦሞ ዞኖች የዘር እና የማዳበሪያ እጥረት ገጥሟቸዋል

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል፣ ድርቁ በርትቶባቸው በነበሩ በኮንሶ እና በደቡብ ኦሞ ዞኖች የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ ዝናም መጣል በመጀመሪ ማሳቸውን ቢያርሱ ፣ የዘር እና የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ገጥሟቸው እየተቸገሩ መኾናቸውን፣ ለአሜሪካን ድምፅ አስታውቀዋል።

የዞኖቹ የግብርና መምሪያዎች፣ ችግሩ መኖሩን አረጋግጠው፣ የታረሰው መሬት ጦም እንዳያድር፣ ምርጥ ዘር እና የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ጥረት እያደረጉ መኾናቸውን ተናግረዋል። በኹለቱ ዞኖች፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎች፣ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል።

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/