በባሕር ዳር ከተማ በቦምብ ፍንዳታ ሦስት ሰዎች ተገደሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በባህር ዳር ከተማ፣ በተለምዶ ዓባይ ማዶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ትላንት ምሽት፣ በአንድ የምግብ እና መጠጥ መሸጫ የንግድ ተቋም ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና ወደ 10 የሚደርሱ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ በአካባቢው የሚገኘው የዐዲስ ዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተወካይ ሜዲካል ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡