በጎዳና ላይ አዳሪ ሕፃናት ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግሥት ተከሠሠ

Your browser doesn’t support HTML5

"ለጎዳና ላይ አዳሪ ሕፃናት እና ወጣቶች ተገቢውን ጥበቃ እና ድጋፍ አላደረጉም፤" በሚል፣ "የሕግ ባለሞያዎች ለሰብአዊ መብቶች" የተሰኘው ተቋም፣ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ መንግሥት ተቋማት ላይ ክሥ መሥርቷል። በፌ/ከ/ፍ/ቤት የመሠረታዊ መብቶች ችሎት በቀረበው ክሥ ሥር፣ በሕፃናቱ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማስቆም ተገቢው እንዲፈጸምላቸው ተጠይቋል። ክሡን ያቀረበው ተቋም ባልደረባ እና በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የሕግ መምህር የኾኑትን ዶ/ር መሰንበት አሰፋን አነጋግረናል።