ወጣቶች ከጦርነትና ከግጭት አስተሳሰብ እንዲወጡ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ሰላምን ለማረጋገጥ የወጣቶችን ጥምረት በመመስረት በሰላም ዙሪያ እንዲወያዩ ዕድል ማመቻቸት እንደሚገባ የዩኤስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር ተናገሩ። በኤጀንሲው አዘጋጅነት የወጣቶች የሰላም ፊስቲቫል በባህር ዳር ከተማ የተካሄደ ሲሆን 3ሺህ ገደማ ወጣቶች በፊስቲቫሉ ላይ ተሳትፈዋል። ወጣቶች ከጦርነትና ከግጭት አስተሳሰብ ወጥተው ልማት ላይ እንዲያተኩሩ ም/ዳይሬክተሩ አደም ሽሚትዝ ጥሪ አቅርበዋል። ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።