በዋግ ኽምራ ዞን እናቶች በወሊድ ምክኒያት በሚገጥም ችግር ሕይወታቸው ማለፉ ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

በዋግ ኽምራ ዞን እናቶች በወሊድ ምክኒያት በሚገጥም ችግር ሕይወታቸው ማለፉ ተገለፀ

አሁንም በህወሓት ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ በተገለፁት፣ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ሥር በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች እናቶች በወሊድ ወቅት በሚገጥም ችግር የተነሳ ህይወታቸው እያለፈ መሆኑ ተገለፀ።

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ላይ ከህወሓት ጋር የሰላም ስምምነት ከተደረሰም በኋላ ከወረዳዎቹ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተናገሩት የብሄረሰቡ ዋና አስተዳዳሪ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፤

“በአሁኑ ወቅት ሰቆጣ የሚገኙት ከ68 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ ድጋፍ እያገኙ አይደለም” ብለዋል።

ስለ ጉዳዩ የተጠየቁ የትግራይ ክልል የተለያዩ የቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው ስለተባለው ጉዳይ የሚያውቁት እንደሌለ ተናግረዋል። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የትግራይ ኃይሎች አመራር 'የትግራይ ሠራዊት በአማራ ክልል አንድም አከባቢ የለም" ብለዋል። “ሆኖም በተጠቀሱ የዋግህምራ አከባቢዎች ግን ሌሎች ታጣቂዎች ሊኖሩ ይችላሉ” ሲሉ ተናግረዋል።

በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት አካባቢውን ነፃ ለማድረግ የፌደራል መንግስቱ እየሰራ መሆኑን እና ችግሩ በሂደት እንደሚፈታ የተናገሩት የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው በፃግብዥ እና አበርገሌ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስና የመንግስት ተቋማት መልሶ ለማቋቋም የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን አመልክተዋል።

በዚህ ዙሪያ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።