የኦሮሚያ ክልል ከተሞች እንደ አዲስ የማደራጀት ውሳኔ ተቃውሞ ቀስቅሷል

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል በጉጅ እና ባሌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፎችን ማድረግ ከጀመሩ ዛሬ አራተኛ ቀናቸው መሆኑን አንዳንድ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

ሰልፎቹ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ሰሞኑን ይፋ ያደረገውን የተለያዩ ከተሞችንና አንድን ዞን እንደ አዲስ የማደራጀት ውሳኔ የተቃወሙ ናቸው።

በተለይ አዲስ ይፋ የተደረገው የምስራቅ ቦረና ዞን በባሌ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች በተጨማሪ በቦረና በጉጂና በባሌ ዞን የሚገኙ ወረዳዎችን በመያዝ መደራጀቱ ቅሬታ አስከትሏል።

በሁለቱ ዞኖች አራተኛ ቀን ያስቆጠረውን የተቋዉሞ ስልፍ በተመለከተ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።