ቆይታ ከቋንቋ መምህርት እና ህጻናት መጽሃፍት አዘጋጅ ምህረት ጌታቸው ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

ምህረት ጌታቸው ነዋሪነቷን በፈረንሳይ ሀገር ያደረገች የቋንቋ መምህርት እና የስነ-ጥበብ ባለሙያ ናት ። ምህረት በተለይ ለውጭ ሀገራት ዜጎች የአማርኛን ቋንቋ ለማስተማር በዘረጋቻቸው መርሀ-ግብሮች ትታወቃለች ። ከዚህ በተጨማሪ ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ህጻናት ስለ ባህላቸው በቀላሉ እንዲያውቁ የሚያግዙ የስዕል መጽሃፍቶችን ታዘጋጃለች ። ከስራዎቿ ጋር የተገናኙ ሀሳቦችን አጋርታናለች ።