የወላይታ ዞን የሕዝበ ውሳኔ ውጤትና ውዝግቡ

Your browser doesn’t support HTML5

የወላይታ ዞን የሕዝበ ውሳኔ ውጤትና ውዝግቡ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29/2015 ዓ.ም ያስፈፀመውን ውሳኔ ሕዝብ ውጤት ይፋ ሲያደርግ የምርጫ ሕግ ጥሰት እንደተፈፀመበት የገለፀውን የወላይታ ዞን ውጤት አለማፅደቁን አስታውቋል።

ቦርዱ በጥር ወር መጨረሻ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች ማለትም ኮንሶ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጌዴኦ፣ በጎፋ እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ማለትም በቡርጂ፣ በባስኬቶ፣ በአሌ፣ በአማሮ፣ በዲራሼ ላይ ያካሄደውን ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ከአንዱ በስተቀር ይፋ አድርጓል።

በወላይታ ዞን የተደረገውን ሕዝበ ውሣኔ በተመለከተ ግን የሂደቱን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ አዳጋች ሁኔታ መፈጠሩ ያስታወቀው ቦርዱ በምርጫ ሕጉና አግባብነት ባላቸው መመሪያዎች መሠረት እንደ ከባድ የአሠራር ጥሠት የሚቆጠሩ ተግባራት በመገኘታቸው ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ማዘዙን አስታውቋል።

በሕዝበ ውሳኔው ሂደት እና ውጤት እንዲሁም በክልሉ ቀጣይ ሁኔታ ላይ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ትንታኔን የሰጡ ባለሞያዎችን ጋብዘናል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።