ፊልም ለማህበረሰባዊ ንቃት ፡-ቆይታ ከጋዜጠኛ እና ፊልም ባለሙያ ማንተጋፍቶት ስለሺ ጋር
Your browser doesn’t support HTML5
መኖሪያውን በጀርመን ሀገር ያደረገው ማንተጋፍቶት ስለሺ በብዙዎች ዘንድ ከሚታወቅበት የጋዜጠኝነት ስራው ባሻገር ዓለም አቀፋዊ ሽልማቶችን ያሸነፈ የፊልም ባለሙያ ነው ።
ከዚህ በፊት "ግርታ " የተሰኘው ፊልሙ የወጣት አፍሪካዊያን የፊልም ፌስቲቫል እና ዛንዚባር ፊልም ፌስቲቫልን ጨምሮ በአራት ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ አሸናፊ ከመሆኑ ባሻገር ትልቅ ክብር የሚሰጠው ፣ "የአፍሪካ ኦስካር " ተብሎ በሚጠራው የፓን አፍሪካ የፊልም እና ቴሌቭዥን ፌስቲቫል ላይም ዕጩ ሆኗል።በተለይ ማህበረሰባዊ አንድምታ ባላቸው አጫጭር ፊልሞች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ማንተጋፍቶት ፣በቅርቡ "የበረንዳው ንጉስ" የተሰኘ አጭር ፊልም ለተመልካች አቅርቧል ።
ይህ ፊልም የካሊፎርኒያ ሲሊከን ቫሊ የአፍሪካ ፊልም ፌስቲቫልን ጨምሮ በተለያዩ ከፊልም ጋር ተያያዥ በሆኑ መድረኮች ላይ እየታየ ይገኛል። አዲሱን ፊልሙን መነሻ አድርገን ከማንተጋፍቶት ጋር ተያያዥ ሀሳቦችን መዘናል።