"ቻት-ጂፒቲ" በረከቶቹ እና ተያያዥ ስጋቶች ፣ የባለሙያ ማብራሪያ
Your browser doesn’t support HTML5
ሰዎች የሚሿቸውን መረጃዎች እጅግ በላቀ ፍጥነት የሚያቀርበው፣ ለጥያቄዎቻቸው አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጠው "ቻት ጂፒቲ" አገልግሎት፣ ሰዎች በራሳቸው ጥረት ለመፈጸም ጊዜያት የሚፈጁባቸውን ስራዎች ሳይቀር ከመቅጽበት በመከወን ረገድ አድናቆትን አግኝቷል። ለመሆኑ ይሄ የዓለምን መልክ እንደሚቀየር የተነገረለት የቴክኖሎጂ ውጤት ፋይዳው እና ስጋቶቹ ምን ይመስላሉ ? በጉዳዩ ላይ ሙያዊ እይታቸውን እንዲያጋሩን ፣ "ኢቫንጋዴ ቴክ" የተሰኘው የቴክኖሎጂ እና የትምህርት ማዕከል መስራች አዱኛ በቀለን ጋብዘናል ።