ራስን ማጥፋት ለምን?
Your browser doesn’t support HTML5
በደረሰበት የአይምሮ መታወክ ምክንያት ራሱን ሊያጠፋ ሞክሮ በህክምና እርዳታ የተረፈው ሄኖክ አምዴ አካለወርቅ ያለፈበትን ፈተና የሚያሳይ እና ስለአይምሮ ጤና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ 'ወደ ራስ መመለስ' የተሰኘ መፅሃፍ ፅፎ አሳትሟል። የዩቲዩብ ገፅ በመክፈትም ተሞክሮዎቹን ያጋራል፣ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የህይወት ልምዳቸውን የሚያካፍሉ ግለሰቦችን ያነጋግራል። በአንድ ወቅት ህይወቱን ሊያጠፋ የነበረ ወጣት እንዴት እዚህ ሊደርስ ቻለ?